ግማሽ የሚደርሱ ብሪታንያውያን አዋቂዎች ክትባት ማግኘታቸው ተነገረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 26 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚደርሱ ብሪታንያውያን አዋቂዎች የመጀመሪያ ዙር የኮሮና ቫይረስ ክትባት መውሰዳቸው ተነገረ፡፡
የጤና ሚኒስትሩ ማት ሃንኮክ ትልቅ ስኬት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ሀገሪቷ አርብ ዕለት ብቻ 711 ሺህ 156 ዜጎቿን ከትባለች፡፡
በጥቅሉ ለ2 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎቿ ደግሞ ሁለተኛ ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡
በሌላ በኩል ሰሞኑን አንዳንድ የአውሮፓ ሃገራት በደህንነት ስጋት ምክንያት አስትራዜኒካን በጊዜያዊነት ማገዳቸው የሚታወስ ነው፡፡
ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ጣልያን አስትራዜኒካን የደህንነት ስጋት አይፈጥርም በማለት ዳግም ዜጎቻቸውን እየከተቡ እንደሚገኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን