ያለ እድሜ ጋብቻን ጨምሮ ታዳጊ ሴቶችን ከሚገጥሟቸው ችግሮች መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዳጊ ሴቶችን፣ ካለዕድሜ ጋብቻ፣ እርግዝና እና ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደረገ፡፡
የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂና ከዩ ኤን ኤድስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊኒ ቢያንዩማን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ታዳጊ ሴቶች በሚደርስባቸው ችግሮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም ኮቪድ19 በወጣቶችና በሴቶች ላይ እያደረሰ በሚገኘው ተጽዕኖ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ዩ ኤን ኤድስ ከተለያዩ የተመድ ተቋማት ጋር በመተባበር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን የተመለከተ ፕሮግራም ይፋ እንሚደያደርግ ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ውስጥ ከተካተቱት 16 ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ እንደምትገኝበትም ነው የጠቀሱት፡፡
ሚኒስትሯ በበኩላቸው ፕሮግራሙን በተመለከተ ኢትዮጵያ የበኩሏን ሚና እንደምትጫወት ማስታወቃቸውን ከሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!