Fana: At a Speed of Life!

በፌደራል የጋራ ገቢዎች ቀመር መሠረት ላለፉት 8 ወራት ከተሰበሰበው ውስጥ ከ14 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ለክልሎች ተከፋፍሏል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል የጋራ ገቢዎች ቀመር መሠረት ላለፉት 8 ወራት ከተሰበሰበው ውስጥ ከ14 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ለክልሎች ተከፋፍሏል፡፡

ለ22 ዓመታት ሲያገለግል የነበረው የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፌደሬሽን ምክር ቤት በመሻሻሉ ምክንያት ባለፉት 8 ወራት 14 ነጥብ 4 ቢሊየን ለክልሎች እንደሚደርሻቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ስምንት ወራት አንፃር ሲታይ 10 ነጥብ 9 ቢሊየን ወይንም 319 ነጥብ 68 ፐርሰንት ዕድገት እንዳሳየ ተገልጿል፡፡

ገቢው ከኤክሳይዝ፣ ከተርን ኦቨር፣ ከተጨማሪ እሴት እና ከንግድ ትርፍ ግብር ታክሶች ብቻ የተሰበሰበ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የጋራ ገቢው ድርሻ ያደገው በሦስት ምክንያቶች መሆኑንም ነው የተዘረዘረው፡፡

የመጀመሪያው የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በመቀየሩ የተቋሙ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ በመምጣቱ እና ተቋሙ በተቀመጠው የማከፋፈያ ቀመር መሰረት ክፍፍሉን በአግባቡ መስራት በመቻሉ የተገኘ ውጤት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የክልልም ሆነ የፌዴራል የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት እና አጋር አካላት የአሰራር ሥርዓቶችን በመከተል ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.