8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የጊንጪ ማከፋፈያ ጣቢያ ቅዳሜ በይፋ ይመረቃል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የጊንጪ ማከፋፈያ ጣቢያ ቅዳሜ በይፋ ይመረቃል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አብርሃም በላይ የጊንጪ ባለ 230/15 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ተመልክተዋል።
ሚኒስትሩ ማከፋፈያ ጣቢያው ለጊንጪ ከተማና ለአካባቢው ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተገጥመውለታል።
እስከ 100 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ሲኖረው አስር ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት ተብሏል።
ግንባታውን ላርሰን ኤንድ ቱርቦ የተባለ የህንድ ኩባንያ ሲያከናውን ኤምቪቪ ዲከን የተባሉ የጀርመንና ስዊዘርላንድ ኩባንያዎች የማማከር ሥራ መስራታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!