የህዳሴ ግድቡን ማጠናቀቅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ጭምር ነው – አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዓባይን ማልማትና የህዳሴ ግድቡን ማጠናቀቅ ለነገው ትውልድ ከመስራትም በላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ጭምር ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡
የህዳሴ ግድብ 10ኛ ዓመትን በማስመልከት በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ አስተባባሪነት በግድቡ ድርድር ላይ የተሳተፉ፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ምሁራን እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙበት ምክክር ተካሂዷል፡፡
በምክክሩ የህዳሴው ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 79 በመቶ እንደደረሰ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ዶክተር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል፡፡
በቀጣዩ ክረምት ቀጠሮ የተያዘለት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌትም በምንም ዓይነት መልኩ እንደማይራዘም ገልጸዋል፡፡
ምክክሩ የግድቡን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም የሶስትዮሽ ድርድሩ የደረሰበትን ደረጃ ለመግለጥ እና ግብዓት ለመሰብሰብ ብሎም የግድቡን 10ኛ ዓመት ለመዘከር የተዘጋጀ መሆኑን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!