Fana: At a Speed of Life!

አቶ ስብሃት ነጋና ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማን ጨምሮ በ42 ተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ስብሃት ነጋና ዶክተር አዲስ አለም ባሌማን ጨምሮ በ42 ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አቀረበ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ባሳለፍነው ሳምንት አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ መክፈቱን ተከትሎ ተጠርጣሪዎች ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ በፍርድ ቤት መታዘዙ ይታወቃል፡፡
ይሁንና የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ ፣ ዶክተር አብርሃም ተከስተና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔን ጨምሮ በ42 ተጠርጣሪዎች ላይ 50 የቅድመ ምርመራ ምስክር ለማሰማት አቅርቧል፡፡
ከ42 ጠተርጣሪዎች ውስጥ በማይካድራ በተፈፀመው የንፁኃን ግድያ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችም ይገኙበታል፡፡
በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቅድመ ምርመራ ምስክሮች የሚሰሙት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው፡፡
በዚህ መሰረት የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮች ከዛሬ ጀምሮ የማሰማት ሂደቱ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.