በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን የሚገኙ ተፈጥሯዊ ሃብቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ ሩጫ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን የሚገኙ ተፈጥሯዊ ሃብቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ ሩጫ በሮቤ ከተማ ተካሂዷል፡፡
ውድድሩ በክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን መዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አቢዩ ተሰማ ውድድሩ ዞኑ ያለውን ሃብት ለማስተዋወቅ ታስቦ ተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ቱሪዝሙን ለማስተዋወቅ በተለይ ወጣቱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
የባሌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ በበኩላቸው÷ ከዚህ በፊት የነበረው ስርዓት የዞኑን የቱሪዝም ሃብት በሚፈለገው እና ማስተዋወቅ ባለበት ደረጃ አለመተዋወቁን ገልፀው አሁን ግን ኮሚሽኑን ከማቋቋም አንስቶ ስራዎች እየተሰሩ ነው ይህም ጥሩ ጅምር ነው ብለዋል፡ ፡
ውድድሩ 5 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ሲሆን 3 ሺህ ሰዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ዞኑ የሶፍ ዑመር ዋሻና የባሌ ተራሮችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የቱሪዝም መስዕቦች የሚገኙበት ነው፡፡
በአዲስ ታምራት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!