Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጅቡቲ፤ ኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመርን የበለጠ ማሻሻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጅቡቲ በኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመርን የበለጠ ማሻሻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በጅቡቲ የሁለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍ እና የነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር አቡበከር ኦማር ሃዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ሀዲድ ኩባንያ ባጋጠሙት ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ዙሪያ ነው የተወያዩት፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት ቀልጣፋ ፍሰት ለማረጋገጥ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር ማጠናከር እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተው መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ሀዲድ የጋራ ኩባንያ የቦርድ ሰብሳቢም ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.