ቢሊየነሩና የማሜሎዲ ሰንዳውን ክለብ ባለቤት ሞትሴፔ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቢሊየነሩና የማሜሎዲ ሰንዳውን ክለብ ባለቤት ፓትሪስ ሞትሴፔ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኑ።
43ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሽን ጠቅላላ ጉባኤ በሞሮኮ ራባት በተካሄደበት ወቅት ነው ፓትሪስ ሞትሴፔ የተመረጡት።
የፌዴሬሽኑ ታሪክ 7ኛው ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ቢሊየነበሩ ፓትሪስ ሞትሴፔ በጠቅላላ ጉባኤው ታሳታፊዎች ያለምንም ተቃውሞ ለሚጪዎቹ አራት አመታት እንዲመሩ ተመርጠዋል።
በፕሬዚዳንትነት ውድድሩ ላይ ሌሎች ሶስት ግለሰቦች ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም የጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች አንድ አይነት አቋም በማሳየታቸው ሌሎች ተወዳዳሪዎች ከውድድሩ ውጭ ሆነዋል።
በዚህ ምርጫ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ታሳታፊ የነበሩነ ሲሆን አፍሪካውያን ላሳዩት አንድነት ምስጋና አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!