Fana: At a Speed of Life!

 በኒጀር ጦር ሰራዊት ላይ በተፈጸመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 89 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኒጀር ጦር ሰራዊት በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 89 መድረሱ ተነገረ፡፡

ቅዳሜ ዕለት በዋና ከተማዋ ኒያሚ በደረሰው ጥቃት በርካታ የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን  የፀጥታ ምንጮች ለሮይተርስ ገልጸዋል፡፡

በናይጄሪያ የጦር ሰፈር ላይ ታጣቂዎች በጦር ሰራዊቱ ባደረሱት ጥቃት  ቢያንስ የ89 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጸጥታ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

በርከት ያሉ ወታደሮች ሐሙስ በቺንጋዳራ ወዲያውኑ መቀበራቸውን ተከትሎ  የሟቾች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ነው የተገለጸው።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢሱፉ ካታምቤ ከእሁዱ የብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት ስብሰባ  ከተካሄደ በኋላ በሰራዊቱ በደረሰው ጥቃት የሟቾችን ቁጥር አሳውቀዋል፡፡

ጥቃቱ ካለፈው ዓመት ጋር በኒጀር  ከተፈጸመው በአራት እጥፍ ከፍ ያለ ሲሆን፥ ወደ 400 ያህል ሰዎችን ገድሏል ፡፡

ለጥቃቱ እስካሁን  ሃላፊነት የወሰደ አካል  እንደሌለ የገለጹትካታምቤ፥ሰራዊቱ በታጠቁት ቡድኖች ላይ  ጥቃት መሰንዘር እንደሚጀምር አስታውቀዋል ፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.