Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ በኮቪድ 19 ከተያዙት ውስጥ 62 በመቶዎቹ ወንዶች ሲሆኑ 38 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ውስጥ 62 ነጥብ 11 በመቶዎቹ ወንዶች ሲሆኑ 37 ነጥብ 89 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን የአፍሪካ ቀጠና የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በአህጉሪቱ የኮሮና ቫይረስ እንደ ወረርሽኝ መከሰቱ ከተሰማበት ወቅት አንስቶ የ100 ሺህ 943 ሰዎች ሕይወት መቅጠፉን ገልጿል፡፡

እስካሁን በአህጉሪቱ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በወረርሽኙ ተይዘዋል፡፡

ከተያዙት መካከልም 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ያህሉ ወይንም 82 በመቶዎቹ ከበሽታው አገግመዋል፡፡

ድርጅቱ ይፋ እንዳደረገው አህጉሪቱ ውስጥ ደቡብ አፍሪካ ከ1 ሚሊየን 500 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

በቫይረሱ ከተያዙት መካከልም 48 ሺህ 940 ዜጎቿ ህይወታቸውን ሲያጡ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ ከበሽታው አገግመዋል፡፡

በጥቅሉ በአህጉሪቱ ከ30 እስከ 39 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በቫይረሱ በብዛት ከተያዙት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡

በአሁን ወቅት ቫይረሱ ያለባቸው 9 ነጥብ 2 በመቶዎቹ ሲሆኑ በአህጉሪቱ በጥቅሉ የሞት ምጣኔው 2 ነጥብ 5 በመቶ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.