የጌዴኦ ብሄር ዘመን መለወጫ የዳራሮ በዓል ተከበረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ብሄር ዘመን መለወጫ የዳራሮ በዓል በዲላ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡
የእለቱ መርሃ ግብርም በጌዴኦ አባገዳዎች የተከፈተ ሲሆን በበዓሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው፣ የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳዉ እንዲሁም የክልል እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የጌዴኦ ብሄር ዘመን መለወጫ የዳራሮ በዓልን ለማክበርም ከዞኑ አራቱም ማዕዘናት የተውጣጡ የበአሉ ታዳሚዎች በዲላ ከተማ ልዩ ልዩ የአደባባይ ትርኢቶችን አሳይተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!