የኢትዮጵያና ሱዳን መንግስታት የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና ታሪክን መሰረት ያደረገ ስምምነት ሊያደርጉ ይገባል- ምሁራን
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ጉዳይና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ውይይት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተካሔዷል።
በውይይቱ ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ከካርቱም ዩኒቨርሲቲ የመጡ ምሁራን ተሳትፈዋል።
ከሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች ሁለት ምሁራን ፅሑፍ አቅረበዋል ።
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ መነሻ ፅሑፍ ያቀረቡት የስነ ማህበረሰብ ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ቡሻ ታኦ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝቦች የእረስ በርስ ግንኙነት ረጂም ጊዜያትን ያስቆጠረና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል።
ይህንንም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ።
ሌላኛው ጽሑፍ አቅራቢ የካርቱም ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ኦማር አል አሚን መንግስታት የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና ታሪክን መሰረት ያደረገ ስምምነት ሊያደርጉ ይገባል ያሉ ሲሆን ምሁራንም ለሀገራቱ መልካም ግነኙነት መስራት አለባቸው ብለዋል።
ይህን መሰል ውይይቶች እንደሚቀጥሉ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጋሻው አንዳርጌ ጠቁመዋል።
በጳውሎስ አየለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም https://t.me/fanatelevision
ትዊተር https://twitter.com/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!