Fana: At a Speed of Life!

ሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን መስጠት ጀመረች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በዛሬው ዕለት መስጠት ጀምራለች።

1 ሺህ ብልቃጥ ሞዴርና ክትባትን ያገኘችው ሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ግንባር ቀደም ሰራተኞችን ጨምሮ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎቿ ነው መስጠት የጀመረችው።

የመጀመሪያዎቹ እና ቀዳሚዎቹ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተጠቃሚዎች በነፃ እንደሚሰጣቸው ዴይሊ ኔሽን በዘገባው ላይ አስፍሯል።

የሩዋንዳ የጤና ሚኒስቴር የተወሰነ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የተገኘው ከዓለም አቀፍ ተባባሪ አካላት እንደሆነ ገልጿል።

በቀጣይ ሳምታትም ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማቅረብ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በዚህም በመጪዎቹ ሁለት ወራት ሩዋንዳ 996 ሺህ ብልቃጥ አስትራዜኔካ እና 102 ሺህ 960 ብልቃጥ ፋይዘር ክትባቶችን እደምትረከብ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.