ባይደን በሜክሲኮ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ሊፈቅዱ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በሜክሲኮ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ሊፈቅድ ነው፡፡
የአዲሱ ፕሬዚዳንት አስተዳደር በሜክሲኮ የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ በማየት ወደ አሜሪካ የማስገባት ሂደት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀጣዩ ሳምንት ወደ 25 ሺህ የሚጠጉ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን ጉዳይ ማየት እጀምራለሁ ብሏል፡፡
ይህን ማግኘት የሚፈልጉ ስደተኞች በቅድሚያ መመዝገብና የኮቪድ19 ምርመራ ወስደው ነጻ መሆን ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡
የአሁኑ እርምጃ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ እተገብረዋለሁ ያሉት የስደተኞችን ጉዳይ የሚመለከተው የፖሊሲያቸው ማሻሻያ አካል ነው፡፡
ባይደን በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይተገበር የነበረውን እና ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክለውን ህግ መሻራቸው ይታወሳል፡፡
የትራምፕ አስተዳደር ይተገብረው በነበረው የስደተኞች ጉዳይ ህግ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች በሜክሲኮ እንዲቆዩና ጉዳያቸው በአሜሪካ የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት እንዲታይ ያደርግ ነበር፡፡
ይህ አሰራር ጊዜ ከመውሰድ ውጭ ለስደተኞች ምንም አይነት ቀና ምላሽ አይሰጥም በሚል ሲተች ቆይቷል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!