Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቶኒብሌር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከአይሲቲና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቶኒብሌር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከአይሲቲና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂው በመጀመሪያ የትግበራ ጊዜያት ያጋጠሙ ችግሮች እየተወሰዱ ያሉ የመፍትሄ እርምጃዎች ተነስተው ውይይት እንደተደረገባቸው ተጠቅሷል።

ስትራቴጂውን ወደ ተግባር ለመቀየር በተቋም ውስጥ በቡድን የመስራት ልምድን ማዳበርና ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ባለሙያዎቹ የዲጂታል ስትራቴጂውን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የዲጂታል አሰራሮችን በመተግበር የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የተዘጋጀ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.