የብልጽግና ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የ6 ወር የሥራ አፈጸጸም ግምገማ እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የ2013 ዓ.ም የስድስት ወር የሥራ አፈጸጸም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።
በዚሁ ወቅት በክልሎች መካከል የሚስተዋለውን የአፈጻጸም ልዩነት ለማጥበብ በተግባር የመስክ ምልከታዎችን በማድረግ ልምድ እንዲቀስሙ በማድረግ የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑ ተገልጿል።
በስራ ዕድል ፈጠራ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታት ሴቶች በተጨባጭ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው ።
በፖለቲካው መስክ በፌደራል ደረጃ እየተስተዋለ ያለው የሴቶች ተሳትፎ አበረታች ቢሆንም እስከታችኛው መዋቅር መጠናከር እንዳለበት ተመላክቷል።
ስብሰባው እስከነገ የሚቀጥል ሲሆን የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው ሃገራዊ ንቅናቄ አቅጣጫ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!