የአማራ ክልል መንግሥት መሬት የማስለቀቅ ውሳኔ ውክልናን ለወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግሥት “የህዝብን ጥቅም ለማሰጠበቅ” መሬት የማስለቀቅ ውሳኔ ውክልናን ለወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ሰጥቷል።
የክልሉ መንግስት ውሳኔ ተግባራዊ እንዲደረግም በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር የተፈርመ ደብዳቤ ለሚመለከታቸው አካላት ተሰራጭቷል።
በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማም ሆነ የገጠር የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የሚያስችል አዋጅ ቁጥር 1161/201 1 ጸድቆ ሥራ ላይ እንዲውል መደረጉ አይዘነጋም።
የሚኒስትሮች ምክርቤትም ይህንኑ እዋጅ ለማስፈጸም የሚያስችል ደንብ ቁጥር 472/2012 ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣው ደንብ አንቀጽ 48 ንዑስ አንቀጽ 1 ስር በተሰጠው ስልጣን መሠረት አዋጁንና ደንቡን ለመፈጸም ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አጽድቆ ስራ ላይ አውሏል፡፡
የአማራ ክልል መንግሥትም የህዝብን ጥቅም ለማሰጠበቅ መሬት የማስለቀቅ ውሳኔ ውክልናን ለወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ሰጥቷል።
የክልሉ መንግስት ውሳኔ ተግባራዊ እንዲደረግም በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር የተፈርመ ደብዳቤ ለሚመለከታቸው አካላት ተሰራጭቷል።
መሬት ለህዝብ ጥቅም የተፈለገ መሆኑን በከተማው ከንቲባ ኮሚቴ ወይም በወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት በኩል እንዲወሰን ውክልና ተሰጥቷቸዋል።
ይህንኑ ውክልና ዞኖች የወረዳዎችንና የከተማ አስተዳደሮችን አፈጻጸም እንዲከታተሉ ርዕሰ መስተዳደሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!