በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሊትር የምግብ ዘይት የሚያመርተው ፋብሪካ በመጪው እሁድ ይመረቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ የሚገኘው በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር በላይ የተጣራ የምግብ ዘይት ማምረት የሚችለው የፌቤላ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በመጪው እሁድ ተመርቆ ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱ ተገለፀ።
ፋብሪካው 30 ሄክታር በሚጠጋ መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን ከዘይት በተጨማሪ የሰሊጥ ማበጠሪያና ማቀነባባሪያ ፋብሪካ እንዳለውም ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳምጤ ስማቸው ለኢዜአ ገልፀዋል።
ማርጋሪን፣ ሳሙና፣ ፕላስቲክና ካርቶን ማምረቻ ፋብሪካዎችን እንዳካተተ ጠቅሰው፤ በስድስት ዓመታት ግንባታው ለተጠናቀቀው ፋብሪካ ለግንባታ፣ ለማሽነሪ፣ ለግብዓት ማቅረቢያ ተሽከርካሪና መሰል ወጪዎች ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል።
በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት የማምረት አቅም እንዳለው ጠቅሰው፤ “ቅድሚያ ለሀገር ውስጥ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የማረጋጋት ስራ ይሰራል” ብለዋል።
እሴት የተጨመረባቸውን የሰሊጥና ሌሎች ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክም የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!