አስተዳደሩ በ6 ወር ውስጥ ከ596 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ6 ወር ውስጥ ከ596 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
በዚህም የእቅዱን 93 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ የተናገሩት፡፡
ተቋሙ በመጀመሪያ 6 ወራት በዝግጅት ምእራፍ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን በመጥቀስ አሰራሩን ለማዘመን ሰፊ ስራ መስራቱን ገልፀዋል፡፡
ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ15 ሚሊየን ብር ብልጫም እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በቀሪዎቹ 6 ወራትም ያሉትን ክፍተቶች በማረም በማዘጋጃዊ ገቢ ከመሰብሰብ አንፃር የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እና የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት እቅድ ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ አቶ አብዱሰላም መግለፃቸውን ከድሬደዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!