ትሪክቦት ማልዌር አዲስ የጥቃት ዘመቻ መክፈቱ ተነገረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚስጢራዊ የሆኑ የፋይናንስ መረጃዎችን ለመጥለፍ የሚውለው እና “ትሪክቦት” የተባለው ማልዌር አዲስ የጥቃት ዘመቻ መክፈቱ ተገለፀ፡፡
ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ማብቂያ ላይ የማይክሮሶፍት ኩባንያን ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር መሰረተ-ልማቶቹን ከአገልግሎት ውጭ አድርጎበት የነበረዉ ትሪክቦት የተባለው የትሮጃን ማልዌር እንደገና ማንሰራራቱን የበይነ መረብ ደህንነት ተመራማሪዎች ገልጸዋል፡፡
የማልዌር ሶፍትዌሮችን ስጋት በማስወገድ ድርጅቶችን ከበይነ መረብ ጥቃቶች የመከላከል ስራን የሚከውነው ሜንሎ-ሴኪዩሪቲ እንዳስታወቀው÷ “ትሪክቦት” አላስፈላጊ የሆኑ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ የመድህን ዋስትና እና የፍትህ ተቋማት በመላክ የማታለል ሙከራ እየፈጸመ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ከዚህ ቀደም ትሪክቦት ጥቃት ለማድረስ የኢ-ሜይል አባሪዎችን በመላክ ይታወቅ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ብቅ ያለው የማጭበርበሪያ ስልቱን በመቀየር ተጠቃሚዎች የማጥመጃ ሊንኮችን እንዲጫኑ በመገፋፋት እና ለጥቃት ወደሚያጋልጥ ሰርቨር እንዲሄዱ በመጋበዝ መሆኑ ታውቋል፡፡
በመሆኑም ተጠቃሚዎች ከማያውቁት አካል የሚላክላቸውን “የከፍታችሁ ግቡ” የኢ-ሜይል መልዕክቶች የላኪውን ትክክለኛ አድራሻ እስካላወቁ ድረስ የማሳሳቻ ወጥመድ ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል፡፡
“ትሪክቦት” የንግድ ድርጅቶችን እና የሸማቾችን የባንክ አካውንት፣ ሚስጥራዊ መረጃዎች፣ ግላዊ የሆኑ መለያዎችን እንዲሁም እንደ ቢት ኮይን ያሉ የዲጂታል መገበያያዎችን መረጃ ዒላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ የባንክ ትሮጃን መሆኑን ኢመደኤ ዘግቧል ፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!