Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ምቹ እድሎች ለዓለም የማስተዋወቂያ መድረክ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ራይዚንግ ኢትዮጵያ በሚል ዘመቻ በበይነ መረብ በይፋ የተጀመረው የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ምቹ እድሎች ለዓለም የማስተዋወቂያ መድረክ በማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ እና በኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ወይዘሮ ለሌሲ ነሜ በይፋ ተጀምሯል፡፡

በወይይቱ በተለያዩ ሃገራት ኢትዮጵያን ወክለው የተሾሙ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ከ100 በላይ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል፡፡

የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ ኢትዮጵያ በርካታ የማዕድን እምቅ ሃብት ያላት መሆኑንና ይህንን ዘርፍ በተገቢው ልክ ማስተዋወቅና የተሻለ ቴክኖሎጂና አቅም ያለው ባላሃብት መመልመል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ለሌሲ ነሜ በበኩላቸው መንግሥት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው በሚገኙ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በማምረቻው፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን እና መሰረተ ልማት በርካታ እድሎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ባለሃብቶችን ለማበረታታትና አሠራሩን ቀላል ለማድረግ በርካታ የኢኮኖሚና የሕግ ማሻሻያዎች እየተካሄዱ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ትልልቅና ታዋቂ የሆኑ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የማስተዋወቅ ሥራ ከኤምባሲዎች ጎን በመቆም እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በበይነ መረብ የሚካሄደው ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ዘመቻ ዛሬን ጨምሮ ለ13 ቀናት እንደሚቆይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.