በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሃብት ያላስመዘገቡ በየተቋማቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ተጠያቂ እንደሚደረጉ ኮሚሽኑ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሃብት ያላስመዘገቡ በየተቋማቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ተጠያቂ እንደሚደረጉ የፌዴራል የስነምግባርና የጸረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ 197 የሚሆኑ የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች በፌደራል መንግስት ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ አስተዳደሮች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት የሰራተኞቻቸውን ሃብት አስመዝግበው አለማጠናቀቃቸውን አስታወቀ፡፡
በዚህም መሰረት በ109 የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የፌደራል መንግስት የልማት ድርጅቶች፣ በፌደራል ምንገስት ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች፣ 60 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት፣ ክፍለ ከተማና ወረዳዎች እንዲሁም 28 የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር ተቋማትና ቀበሌዎች የሰራተኞቻቸውን ሃብትና ንብረት ሙሉ ለሙሉ ያላጠናቀቁ ናቸው ብሏል ኮሚሽኑ፡፡
ሃብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸው እያወቁ በቸልተኛነትና ፍቃደኛ ባለመሆን ሀብታቸውን ባላስመዘገቡ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ በሕጉ መሠረት ከጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚሽኑ በአፅንዖት አስታውቋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!