የአፍሪካ ህብረት ተጨማሪ 400 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደሚያቀርብ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአፍሪካ ህብረት ለአባል ሃገራቱ የሚሆን ተጨማሪ 400 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንደሚያቀርብ የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል /ሲዲሲ/ አስታወቀ፡፡
የማዕከሉ ዳይሬክተር ጆን ንከንጋሶንግ ክትባቱ የሚገኘው የኦክስፎርዱን አስትራዜኒካ ቀመር በመጠቀም ክትባት ከሚያመርተው ሴረም ከተሰኘ የህንድ ተቋም ነው ብለዋል፡፡
ህብረቱ ከዚህ ቀደም 270 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለአባል ሃገራቱ እንደሚያቀርብ መግለጹ ይታወሳል፡፡
የአሁኑ 400 ሚሊየን መጠን ያለው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሲታከልበት ለአባል ሃገራቱ መልካም ዜና መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡
አፍሪካ 60 በመቶ የሚሆነው ህዝቧን የመከላከል አቅም ለማዳበር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን መጠን ክትባት እንደምትፈልግ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም ከ7 እስከ 10 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ከዚህ ቀደም አፍሪካውያን ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 50 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት እንደሚያገኙ መግለጹ ይታወሳል፡፡
እስካሁን ከአባል ሃገራት መካከል ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ሲይሼልስ እና ጊኒ ዜጎቻቸውን መከተብ ጀምረዋል፡፡
ምንጭ፡-ሲጂቲኤን
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!