በምዕራብ ጉጂ የአባያ ወረዳ ፖሊስ 278 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እጽ ተያዘ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጉጂ ዞን የአባያ ወረዳ ፖሊስ በተሽከርካሪ ተጭኖ ወደ ሞያሌ ሲጓጓዝ የነበረ 278 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እጽ መያዙን አስታወቀ።
የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሻምበል ደረሰ ለኢዜአ እንዳሉት፤ አደንዛዥ እጹ የተያዘው ከሀዋሳ ወደ ኬንያ ሞያሌ ከተማ እየተጓጓዘ በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ሰመሮ ቀበሌ ሲደርስ ነው።
ፖሊስ አደንዛዥ እጹን ሲጓጓዝበት ከነበረው ተሽከርካሪ ጋር ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ይዞ ምርመራ እያደረገ ሲሆን፤ እጹን በማዘዋወር የተጠረጠረውን ግለሰብ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ለመቆጣጠር ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ አያኖ አለማየሁ በበኩላቸው ህገ ወጥ እንቅስቃሴን ለመከላከል ከግለሰብ እስከ መንግስት ተሽከርካሪዎች የተጠናከረ ፍተሻና ቁጥጥር በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የአካባቢው ህብረተሰብ ህገ ወጥ እንቅስቃሴን በማጋለጥ ረገድ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ በመቀጠል ከወረዳው ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ እንዲሰራ መጠየቃቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!