ጠ/ሚ ዐቢይ የገናን በዓል ከአረጋውያን፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ጋር በአንድነት ፓርክ አከበሩ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ጠዋት የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ከአረጋውያን፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ጋር በአንድነት ፓርክ አክብረዋል።
በዚህ ወቅትም ቁሳዊ ሃብት ብቻውን ባለጸጋ አያደርግም፤ብልጽግና መስጠት እና መካፈልን የሚጨምር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።
መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው፣