የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲየኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ፈቃድ በማግኘት ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደርጃ ማደጉን አስመልክቶ የማብሰሪያ ስነ ስርዓትተካሂዷል።
በዚህ ስነስርዓት ላይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነአ ያደታ፣የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ዶክተር ር ጌዲኦን ጢሞቲዮስ ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ጨምሮ ሌሎች እንግዶችም ተገኝተዋል።
ተቋሙ በንጉስ አጼ ሀይለስላሴ ዘመን 1939 የኢትዮጽያ ፖሊስ ኮሌጅ ሆኖ የተመሰረተ ሲሆን÷ ለ60 አመታት በኮሌጅነት በመቀጠል ከ1999 ጀምሮ እስከ 2013 ታህሳስ 4 ድርስ ደግሞ የኢትዮጽያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሆኖ ቆይቷል።
ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በተሰጠው ማርጋገጫ መሰርት ከታህሳስ 5 2013 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ ደርጃ በማግኘቱ አሁን የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ሆኗል።
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ እስካሁን በሰርተፊኬት ፣በዲፕሎማና በድግሪ ብቁ የፖሊስ መኮንኖችን ሲያስመርቅ መቆየቱም ነው የተገለጸው።
አሁንም ወደ ዩኒቨርሲቲ ማደጉ ብቁና ከዘመኑ ጋር የሚራመድ ፖሊስ ለማፍራት እንዲሰራ ያስችለዋልተብሏል።
በዝግጅቱ ላይ የፖሊስ ኮሌጁ ከምስርታ ግዜ አንስቶ አሁን የደርሰበትን የቀጣይ ጉዞውን ደርጃ የሚያሳይ ዶክመንተሪ ቀርቧል።
በአዳነች አበበ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!