በኦስትሪያ መንግስት ላይ ከባድ የሳይበር ጥቃት መፈፀሙ ተገልጿል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ላይ ከባድ የሳይበር ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል።
የሳይበር ጥቃቱ በሌላ ሀገር አማካኝነት የተቀነባበረ ሳይሆን እንዳልቀረ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታውቋል።
ጥቃቱ የተፈፀመውም አረንጓዴ የተሰኘው የኦስትሪያ ፓርቲ ከወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት ለመመስረት የቀረበው ሃሳብ በደገፈበት ቀን ነው ተብሏል።
የሳይበር ጥቃቱ ትናንት ማታ የተጀመረ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል።
የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጠው መግለጫ፥ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ክስተቱን በፍጥነት በመረዳት አስፈላጊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል።
ይን እንጂ መስሪያ ቤቱ በተፈጸመው የሳይበር ጥቃት ምን ያህል ጉዳት ስለመድረሱ ያለው ነገር የለም።
በሌላ በኩል አሁን ላይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ከማድረግ ባለፈ ወደ ፊት ሊፈጸም የሚችልን የሳይበር ጥቃት መቶ በመቶ መቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ ተመላክቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ የአውሮፓ ሀገራት በርካታ የሳይበር ጥቃቶችን እያስተናገዱ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
ምንጭ ፦ቢቢሲ