Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት በትምህርት ቤቶች የኮቪድ19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ መተግበራቸውን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውን ተከትሎ የኮቪድ19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ መተግበራቸውን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ኮቪድ19 መከሰቱን ተከትሎ ባለፈው አመት መጋቢት ወር ላይ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ይታወሳል፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ተማሪዎች በቤታቸው የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ከትምህርት የራቁበትን ጊዜ ለማካካስ ሲሞክሩ ቆይተዋል፡፡

ባለፈው መስከረም ወር ላይም መንግስት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲከፈቱና ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

አሁን ላይም ትምህርት የተጀመረ ሲሆን ድርጅቱም ከጤና እና ትምህርት ተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ በቅርበት እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

ይህም በትምህርት ቤቶች የቫይረሱን ስርጭትና መስፋፋት እንዲሁም የተማሪዎችን እና አስተማሪዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ያለመ መሆኑንም ነው ድርጅቱ የገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ከአስተማሪዎች ውጭ ያሉ የትምህት ቤቱን አባላት ተጋላጭነት በመቀነስ የማህበረሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑንም ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ቦሪዬማ ሃማ ሳምቦ ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው ጋር ተያይዞ ጥብቅ የሆኑ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ቤቶች ዳግም መከፈትም የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል የሚመከሩ ባህርያትን ለመተግበርና ወጣቶችን ወደለውጥ መሪነት ለማብቃትና ለመጠቀም መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.