Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ የወጪ ንግድ ግኝትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የማምረቻ ዘርፉ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታትና የወጪ ንግድ ግኝትን ለማሳደግ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ የሃገሪቱ ኢንዱስትሪዎች ከአቅም በታች እያመረቱ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ጠንካራ ስራ ለመስራት ጠንካራ ፖሊሲ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

እየተዘጋጀ ያለው የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተግባራዊ ሲደረግ ለሃገሪቱ ኢንዱስትሪዎች ችግር መፍትሄ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ዘርፍ ማስፋፊያ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት በመንግስት ተቋማት በኩል ያለው የመናበብ ችግር እና የተንዛዛ ቢሮክራሲ ኢንዱስትሪውን እንደሚጎዳውና በቀጣይ ትኩረት እንደሚፈልግ አውስተዋል፡፡

የንግድ ሚዛኑን ተመጣጣኝ ለማድረግ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሳደግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው መባሉንም ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.