Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያስተናገደችዉ የአኖካ ጉባኤ ዝግጅት ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያስተናገደችዉ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ጉባኤ ዝግጅት ስኬታማ እንደነበር ተገለፀ፡፡
የአኖካ ጉባኤ እና የጠቅላይ ሚኒስትር አዐይ አሕመድ የሽልማት እና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ፣ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸዉ ድንቁ፣ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ እና የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጆች፣ የሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች እና የስፖርት ሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ2020 ቶኪዮ ከፍተኛ በጀት ዕቅድ እዲያዝ ማድረግ እና ስፖርትን ለሠላም መሳሪያነት ተጠቅሞ በሃይል የመጣውን ወታደር ፑሽ አፕ አሠርቶ ማረጋጋት መቻል ለአኖካ ከፍተኛ ሽልማት እንዳበቃቸው ተናግረዋል።
ሽልማቱም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ክብር ነው ብለዋል።
በመድረኩም ለጉባኤው መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላት ሰርቲፊኬት እንደተበረከተላቸው ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.