የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የህዝቡን መብትና ጥቅም ለማስከበር እየሰራ መሆኑን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ህዝብ መብትና ጥቅም ለማስከበር እየሰራ መሆኑን ገለጸ።
ይህንን ለማረጋገጥም ፖሊሲና ፕሮግራሞችን ቀርጾ ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱን ነው አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅትም በተጨባጭ ለህዝብ መብትና ተጠቃሚነት እየሰራ እንዳለ ዛሬ ባወጣው መግለጫው ገልጿል።
የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ልማትን ለማፋጠን እና ስርአት ለማስከበር በትጋት እንደሚሰራም ነው የገለጸው።
መንግስት በበጀት አመቱ የተነደፉ እቅዶችን በአግባቡ በመተግበር ተጠቃሚነትን ያረጋግጣልም ብሏል።
በገጠር ልማት ለግብርና ትኩረት በመስጠት በተጨባጭ የህዝቡን ኑሮ የሚቀይር ስራ ይሰራል ብሏል የክልሉ መንግስት በመግለጫው።
ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቋቋም ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶታልም ነው ያለው።
የቢራ ገብስን እና ስንዴን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ካለፈው የምርት ዘመን የተሻለ ስራ ለመስራት ዝግጅትና ተግባር ያለ መሆኑን ገልጿል።
በመኸር ምርት በክላስተር ለማምረት ግብአቶችን በወቅቱ ለማቅረብ እና ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት ተሰጥቷል ብሏል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት።
የአንበጣ ወረርሽኝን በርብርብ መመከት እንደቻልነው ሁሉ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ምርትን እንዳያበላሽ መረባረብ ያሻል ሲል ጥሪ አቅርቧል።
በጋውን አርሶ አደሩ በመስኖ ልማት እንዲሳተፍ ይደረጋልም ነው ያለው።
ለእቅዱ መሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!