የሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሎምፒክ 60ኛ ዓመት የማራቶን ድል መታሰቢያ በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሎምፒክ 60ኛ ዓመት የማራቶን ድል እና ከሜልቦርን (1956) እስከ ሪዮ ዲጄኔሮ (2016) ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ተሳትፈው ሃገር ያኮሩ ጀግኖች የሚዘከሩበት መርሃ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል መካሄድ ጀምሯል ።
በፕሮግራሙ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ እና የፕሮግራሙ አካል የሆኑ የኦሊምፒክ ጀግኖች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።