Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ የቀድሞ ጀግኖች አትሌቶች የአበባ ማስቀመጥ ስነ ስርዓት እና የሃውልት ምረቃ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኢትዮጵያ የቀድሞ ጀግኖች አትሌቶች የአበባ ማስቀመጥ ስነ ስርዓት እና የሃውልት ምረቃ ተካሄደ፡፡
ለሻምበል አበበ ቢቂላ እና ሻምበል ማሞ ወልዴ መካነ መቃብር በሚገኝበት በቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን የአበባ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት የተከናወነ ሲሆን ÷የሻምበል ማሞ ወልዴ ሃውልት ፈርሶ የነበረው በድጋሚ ተሰርቶ ምረቃው ተከናውኗል፡፡
እንዲሁም ለሻምበል ምሩፅ ይፍጠር እና ለስመጥሩ አሰልጣኝ ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ እና አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ መካነ መቃብር ላይ በመገኘት የአበባ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡
የአበባ ማስቀመጥ ስነ ስርዓት እና የሃውልት ምረቃው ላይ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሌያስ ሽኩር ፣ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ም/ፕረዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊወርጊስ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሪዚዳንት እና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ አቶ ኤልያስ ሽኩር እና ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ባስተላለፋት በመልክት ጀግኖችን ማሰብና መዘከር ለተተኪዎች የሞራል ስንቅ ነው ብለዋል፡፡
የሻምበል አትሌት አበበ ቢቂላ 60ኛ ዓመት የሮም ኦሎምፒክ የማራቶን ድል እና ከሜልቦርን እስከ ሪዮ የኦሎምፒክ ባለድሎች እና ተሳታፊዎችን የሚዘክር መርሃግብር ከታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተዘጋጅቶ እየተካሄደ ይገኛል ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.