Fana: At a Speed of Life!

ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ያሉ ሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 2፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ከታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

መንግስት የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል  የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአውሮፕላን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር 25 ብር ከ37 ሳንቲም በዓለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 10 ሳንቲም ጨምሮ በሊትር 25 ብር 47  ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

በአለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.