“ኢትዮጵያ አንድ ሆነች ጁንታው ለብቻው ቀረ!” – ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁንታው ባደረገው ልክ የሰው አውሬ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበር ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴ በተገኙበት በአዲስ አበባ ለመከላከያ ሰራዊት ለተደረገ ድጋፍ የእወቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ባደረጉት ንግግር ጁንታው ባደረገው ልክ የሰው አውሬ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበር ብለዋል።
ጁንታው ሁለት አመት የተዘጋጀበትን ውጊያ እኛ በሁለት ሳምንት ማሸነፍ ችለናል ብለዋል።
አሁን ሁሉም ነገር አልቆለታል የጁንታው ቡድን ከመኪና ወርዶ እግረኛ ሆኗል፤ አሁን እግረኛ በማሳደድ ላይ ነን ብለዋል ጀነራል ብርሃኑ።
ህዝብ ያለ ሰራዊት ሰራዊትም ያለ ህዝብ መኖር አይችሉም ያሉት ጀነራሉ በህዝብ ድጋፍና እገዛ ሰራዊቱ አሸናፊ ሆኗል ብለዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን