የህወሃት ጁንታ በሰራዊት አባላት፣ ሴቶችና ህፃናት ላይ መኪና በመንዳት ጭካኔውን አሳይቷል- የሰራዊቱ አባላት
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የህወሃት ጁንታ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ሴቶችና ህፃናት ላይ በህይወት እያሉ የሲኖትራክ መኪና በመንዳት የጭካኔውን ጥግ ማሳየቱን የሰራዊቱ አባላት ተናገሩ።
የ7ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ አሸማጋይ በመምሰል ሰራዊቱን እጅ እንዲሰጥ በማድረግ ታሪክ ይቅር የማይለው የክህደት ወንጀል መፈጸሙንም ገልጸዋል።
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ጁንታው ያደራጀው ታጣቂ ሃይል በሰሜን ዕዝ የሰራዊት አባላት ላይ ጥቃትና ዘረፋ መፈፀሙ ይታወሳል።
በሰሜን ዕዝ የጥገና ክፍል አባል ሃምሳ ዓለቃ ደረጀ አንበሳ “የጁንታው ልዩ ሃይልና ሚሊሻዎች በግራና ቀኝ መሳሪያ በመደገን በአስፓልት ላይ መብራት የሌለው ሲኖትራክ ዚግዛግ እየነዱ ብዙዎችን በመግጨት ገድለዋል” ይላሉ።
“የጁንታው ቡድን ሰብል ለሰበሰብንበት፣ አንበጣ ላባረርንበት ህፃናትን ላስተማርንበት ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ላስገነባንበት ምላሽ ጠላት አድረጎን ጥቃት ፈጸመብን” ብለዋል።
በሰው ልጅ ላይ ከነነፍሱ እያለ በከባድ መኪና እየነዳ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ በብዙዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ገልጸዋል።
የሰባተኛ ክፍለ ጦር አባል ሃምሳ አለቃ ወንድማገኝ ወልደገብርኤል “የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሃይላይ ገብሩ እንደ ቄስ ጠምጥሞ የሃይማኖት አባት በመምሰል ሰራዊታችንን በማታለል ክዷል” ብለዋል።
“ቄስ መስሎ ራሱን ለውጦና ጭንቅላቱ ላይ ጠምጥሞ አስታራቂ መስሎ በመቅረብና በማስመታት ክህደት ፈፅሞብናል” ነው ያሉት።
የጁንታው ቡድን የክህደቱ ጥግ ማሳያ በማድረግ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ በጭካኔ በላያቸው ላይ ከባድ መኪና እየነዳ ሲገድላቸው በአይናቸው ማየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!