Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን አደረጃጀት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 29 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን አደረጃጀት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ከሃይማኖት አባቶች፣ ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር፣ መረዳጃ ማኅበራት፣ የህዳሴ ምክር ቤት፣ የቢዝነስ ኮሚዩኒቲ እና የሆቴሎች ማኅበራትን ከወከሉ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

ውይይቱ የተጀመረው በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ በተፈፀመው ጥቃት እንዲሁም በትግራይ ክልል ህግና ሥርዓትን በማስከበር ሂደት ላይ ውድ ህይወታቸውን ላጡ የሠራዊቱ አባላትና ወገኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው፡፡

በውይይቱ ወቅት በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ህግ የማስከበሩ ተግባር ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ፣ እንዲሁም ለመከላከያ ሠራዊቱ እስካሁን ስለተደረገ ድጋፍ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የትግራይን ክልል እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸውን የሠራዊቱ አባላትና ቤተሰቦች መልሶ ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የማህበረሰቡ ተወካዮች ለዚህ የመልሶ ማቋቋም ተግባር የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ከማሰባሰብ አኳያ ከአንድ ወር በፊት በተዘጋጀው መድረክ ላይ ቦንድ ለመግዛት ቃል ከተገባው ውስጥ እስካሁን ከ50 ሺህ ዶላር በላይ ተሰብስቦ ገቢ ተደርጓል።

ከዚህ ባለፈም የህዳሴ ግድቡን ማጠናቀቅ ማለት ከአባይ ውሃ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ጫና እና ሥጋት ማቃለል መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የሚወክሏቸውን የማህበረሰብ አባላት የማስተባበር ስራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.