ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድህረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።
ይህ ተግባር ሦስት መልኮች አሉት ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
እነዚህም ሰብአዊና ማኅበራዊ ድጋፍ፣ የተጎዳውን መሠረተ ልማት መልሶ መገንባት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማስጀመር መሆናቸውንም ገልጸዋል።
እነዚህ ሥራዎች በስፍራው በተገኙ ቡድኖች አማካኝነት ተጀምረዋልም ነው ያሉት።
የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎትም እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን የማኅበረሰብ ክፍሎች በመደገፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አንድ ሆነን የተቋረጠውን እናስቀጥላለን፣ የፈረሰውን እንገነባለን፣ የነገውንም እናለማለን ሲሉ በማህበራዊ ገጻቸው ገልጸዋል።