Fana: At a Speed of Life!

15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል በባህርዳር ከተማ በውይይት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል ኢ-ህገመንግስታዊ እንቅስቃሴን ማስቆምና የህግ ማስከበር ተልዕኮ ለህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን ያለው ፋይዳ በሚል መሪ ቃል በባህርዳር ከተማ በውይይት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በውይይቱ የመከላከያ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትዕግስትና ጥበብ፣ በመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሀይል እና በህዝቡ ትግል አለድል ስለበቃን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

የህወሓት ከሃዲ ቡድን የሀገር ክብርና የሉዓላዊነት መገለጫ የሆነው መከላከያ ሰራዊት ግፍና በደል ፈፅሟል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ህወሓት የአማራን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል የማሳደድ ስራ ሲሰራ ቆይቷልም ብለዋል አፈ ጉባዔዋ፡፡

በተጨማሪም ህወሓት ንፁሀን ዜጎችን ሲገድልና ሲያስገድል ቆይቷል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“በዚህም የብሄር ብሄረሰቦችን በዓል ዛሬ ስናከብር ለህዝባችን ፍትህና ዴሞክራሲ በሚያጎናፅፍ ሁኔታ” መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

ለተንቀሳቃሽ ምስሎች  የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.