Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስወነጨፈቻትን ˝ኢት አር ኤስ ኤስ 1˝ ሳተላይት በይፋ ከቻይና ተረከበች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይናው ታዩዋን ከተማ የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከል ወደ ህዋ ያስወነጨፈቻትን ˝ኢት አር ኤስ ኤስ 1˝ ሳተላይት በይፋ ከቻይና ተረከበች።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ሳይተላይቷን ማስወንጨፏ የሚታወስ ነው።

የሳተላይቷ ይፋዊ ርክክብ ቀደም ብሎ በሁለቱ ሀገራት የዘርፉ መስሪያ ቤቶች በኩል ለማከናወን ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ በፈጠረው የጉዞ መስተጓጎል ምክንያት ሳይከናወን መቆየቱ ተጠቁሟል።

በዚህም በሁለቱ ወገን በተደረሰ ስምምነት በቻይና ኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ እንዲረከቡ በተወሰነው መሰረት በትናንትናው ዕለት በቻይና ስፔስ ቴክኖሎጂ አካዳሚ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ርክክቡ ተፈፅሟል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

 

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.