በሩሲያ ኢትዮጵያን የተመለከተ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ኢትዮጵያን የተመለከተ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ።
በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተካሄደውን ፎረም በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያዘጋጀው ነው።
ፎረሙ በኢትዮጵያ ያሉ መልካም የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም ከአካባቢው ሃገራት በተለይም ከሩሲያና ቤላሩስ ጋር ኢንቨስትመንት እና ንግድን በመሳብ የሃገራቱን የቢዝነስ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ለፎረሙ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ አድርገዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግድ ኢንቨስትመንቶችን በተመለተ ገለጻ ማድረጋቸውን በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!