የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደማቸውን ለገሱ።
የደም ልገሳውን ያደረጉት የህወሃት ጁንታ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ህግ በማስከበር ዘመቻ ላይ ያለውን ሰራዊት ለመደገፍና አጋርነታቸውን ለማሳየት መሆኑ ተገልጿል።
የደም ልገሳ መረሃ ግብሩ እስከታችኛው የፓርቲው መዋቅር ቀጣይነት ያለው መሆኑም ታውቋል።
በደም ልገሳው የተሳተፉ የጽህፈት ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች መከላከያ ሰራዊቱ አገርን ህዝብን ለመጠበቅ እያደረገ ያለውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ለመደገፍ መሆኑን ገልጸዋል።
የደም ልገሳ ማድረጋቸው ለሰራዊቱ ያላቸውን ፍቅርና አጋርነት ለማሳየት መሆኑንም ተናግረው ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉም ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።