ፌስቡክ ሰራተኞቹን ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ አስገድዷል የሚል ክስ ቀረበበት
አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ፌስቡክ ሰራተኞቹን ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ አስገድዷል የሚል ክስ እንደቀረገበበት ተገለጸ፡፡
የፌስቡክ ኩባንያ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ሰራተኞቹን ከቤት ሆነው እንዲሰሩ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ግዴታ መጣሉን በመቃወም በኩባንያው በይዘት ግምገማ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ክስ አቅርበዋል፡፡
በዓለም ዙሪያ ከ2 መቶ የሚበልጡ የፌስቡክ ሠራተኞች የኮሮና ቫይረስ የመያዝ አደጋ ቢኖርም ወደ ስራ ገበታችን እንድንመለስ ተገደናል በሚል ፌስቡክን ከሰውታል፡፡
ክሱ በቀረበበት ደብዳቤም ትርፍ ለማስገኘት ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል ሰራተኞቹ፡፡
ፌስቡክ በበኩሉ አብዛኛው የይዘት ገምጋሚዎች በየቤታቸው እየሰሩ ነው ሲል አስተባብሏል ፡፡
የኩባንያው ቃል አቀባይ 15 ሺህ የሚሆኑት አብዛኛው ዓለም አቀፍ የይዘት ገምጋሚ ሰራተኞች በየቤታቸው እየሠሩ የቆዩ ሲሆን ይህም ይቀጥላልም ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
ፌስቡክ ሰራተኞቹ እስከ 2021 ክረምት ድረስ ከቤት ሆነው መሥራት እንደሚችሉ መናገሩን ዘገባው አስታውሷል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ