Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ለጥፋት ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሐረሪ ክልል ሐኪም ወረዳ ለጥፋት ዓላማ ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ምክትል ኮማንደር ናስር ከዲር እንደገለጹት በወረዳው ጥፋት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል::

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት ከጸጥታ ሃይሉ፣ከወረዳው መስተዳድር፣ከንዑስ ቀበሌ አመራር፣ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በአስራ አምስቱም ተጠርጣሪዎች መኖርያ ቤት በተደረገው ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል።

የጦር ሜዳ መነጽር፣ የራዲዮ መገናኛ፣ ፎቶ ካሜራ፣የጦር መሳርያ መያዣ ቁሳቁሶች፣20 የሚደርሱ ሲምካርዶች፣ የጦር ሜዳ የመጀመርያ ህክምና መስጪያ ቁሳቁሶች ከተጠርጣሪዎቹ የሽብር መልዕክተኞች የተያዙ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም የተለያዩ መታወቂያዎች፣ የባንክ ቤት ቼክና ደብተር፣ ላፕቶፖች፣ የጸረ ሽምቅ ውጊያ ማስተማሪያ መጽሃፎችና ሌሎች ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ናስር ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.