በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 75 ሚሊየን ብር በጥሬ እና በአይነት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር፣ አርሶአደሮች፣ ባለሃብቶች፣ አመራሮች፣ ሰራተኛች እና ነዋሪዎች 75 ሚሊየን ብር በጥሬ እና በአይነት ለመከላከያ ሰራዊት እና ድጋፍ አደረጉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የህወሓት ጁንታን ወደ ህግ የማምጣት ተዕልኮውን በድል በመወጣት ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ሀይል እና የሚሊሻ አባላት የአካባቢው ህብረተሰብ አጋርነቱን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።
በዚሁ መሰረት 8 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ፣ ግምታቸው 12 ሚሊየን ብር የሚሆን 88 ሰንጋ፣ 84 በግና ፍየል፣ የወር ደመወዝ እና ሌሎች ድጋፎችን ጨምሮ በድምሩ 75 ሚሊየን ብር በጥሬ እና በአይነት አሰባስበው ርክክብ አካሂደዋል።
ይህን ሁሉንም አሰባስቦ በጋራ ያቆመን፣ የፍቅር እና የአንደነት ጉዞ አደንቃለሁ ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።