ተቋማት የሳይበር ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ ሊወስዱ የሚገባቸዉ የመፍትሄ ሃሳቦች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተቋማት የበይነ መረብ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ ሊወስዱ የሚገባቸው የመፍትሄ ሃሳቦችን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በየትኛዉም ዘርፍ፣ በየኛውም ስፍራ የሚገኙ ግዙፍም ሆኑ አነስተኛ ተቋማት በማንኛውም ወቅት የበይነ መረብ ጥቃት ሰለባ የመሆን እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ያመለክታሉ።
በመሆኑም ተቋማት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የበይነ መረብ ጥቃት ለመከላከል ሊወስዱ ከሚገባቸው የመፍትሄ አማራጮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
-ተቋማዊ የበይነ መረብ ደህንነት ስትራቴጂ እና ፖሊሲዎችን መንደፍ እና መተግበር
-የተለያዩ የበይነ መረብ ስጋት አስተዳደር፣ የአደጋ መልሶ ማገገሚያ እና የስራ ቀጣይነት ፕሮግራሞችን መቅረጽ እና መተግበር
-የበይነ መረብ ደህንነት የስራ ክፍልን ከዋናው አደረጃጀት ጋር በማይጋጭ መንገድ ማቋቋም፤
-በተፈጠረው አደረጃጀት ላይ አስፈላጊውን እና ብቁ የሆነ የሰው ሀይል በመመደብ ስራዎችን መስራት
-ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ቴክኖልጂዎች ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች መቀየር ወይም ማዘመን
-በተቋማት የወሳኝ አቅም በይነ መረብ ደህንነት መለኪያን ተግባራዊ ማድረግ መሆናቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።