Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል የበረሃ አንበጣ ለመከላከል 27 ድሮኖች ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የእስራኤል መንግስት የበረሃ አንበጣ ለመከላከል የሚያግዙ 27 ድሮኖች ድጋፍ ማድረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ከድሮኖቹ በተጨማሪ ሁለት ጄኔሬተሮችንም ለግሰዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ድሮኖቹን በመጠቀም በሌሊት ርጭት በማድረግ የመከላከል ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡

በድሮኖቹ በመታገዝም የዳሰሳ ጥናት በማድረግ መረጃዎችን በመሰብሰብ ውጤታማ የመከላከል ስራ ለመስራትም ይረዳል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራፍ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል በድሮኖች የታገዘ መረጃ የመሰብስብና በሌሊት ርጭት በማካሄድ የመከላከል ስራ ለመስራት እንደሚያግዙ ነው የተናገሩት፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.