Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ የዜጎቿን የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ በመፈተሽ ግብር ሰዋሪዎችን ልትለይ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ የዜጎቿን የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ በመፈተሽ ግብር ሰዋሪዎችን ልትለይ እንደሆነ ተገለፀ፡፡

ይህም ባለፈው ሳምንት ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወጣው ሕግ አካል ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በገፃቸው ላይ የሚለጥፉትን  የግል መረጃ ዝርዝር  በማየት  ነው ግብር የከፈለ እና ያልከፈለ የሚለየው፡፡

እርምጃው የዜጎች ራስን በነፃነት የመግለጽ እና የግላዊነት መብት ላይ ጫና ሊያሳድር ቢችልም ድንጋጌው የሚተገበርበት ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ተብሏል።

ከቅድመ ሁኔታዎቹ አንዱ በሚስጥራዊ ይለፍ ቃል የተቆለፉ ገጾችን ሰብሮ አለመግባት ነው፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሕዝብ ይፋ የተደረጉ መረጃዎችን መጠቀም እንደሚችል ነው የተነገረው።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል ሕጉ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል።

የበጀት ሚንስትሩ ጄራልድ ዳርማኒን በበኩላቸው አጭበርባሪዎችን የምንገታበት አንድ መንገድ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.