Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በወታደራዊ ሕግ የሚያስጠይቅ ከፍተኛ ወንጀል ነው- የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ወለድ 102ኛ ክፍለ ጦር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ወለድ 102ኛ ክፍለ ጦር ሰሜን ዕዝ ላይ የክልሉ ልዩ ሃይል የፈጸመው ጥቃት በእጅጉ አሳፋሪ፣ አገራዊ ክህደትና በወታደራዊ ሕግ የሚያስጠይቅ ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን ገልጻል።

ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ነፃነታቸውን አስጠብቀው ከኖሩ ጥቂት አገራት አንዷና እንደነፃነት ቀንዲል የምትታይ የመላው ጥቁር ሕዝብ መመኪያ ናት።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራትም ሆነ ከአውሮፓውያን በተለያየ ጊዜ የተቃጣባትን ጥቃት መክታ መመለስ ብቻ ሳይሆን፤ የሌሎች አገራትን ሰላም ለማስጠበቅ በተለያዩ የዓለም አገራት ዘምቶ ታሪክ የሚያወሳው ጀብድ ፈጽሟል።

ይሁንና በተጠናቀቀው ሳምንት መጀመርያ ላይ ትግራይ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የክልሉ ልዩ ሃይል የፈጸመው ጥቃት በእጅጉ አሳፋሪ፣ አገራዊ ክህደትና በወታደራዊ ሕግ የሚያስጠይቅ ከፍተኛ ወንጀል ሆኖ አግኝተነዋል።

ይህንን ከጀርባ የተፈጸመ አስነዋሪ ደባ፥ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ወለድ 102ኛ ክፍለ ጦር አባላት አምርረን እንደምናወግዘው እየገለጽን ትናንት ለሉዓላዊነቷ ለደማንላት ውድ አገራችን ዛሬም በግንባር ቀደምትነት እንደምንቆም ለመላው ሕዝባችን እንገልጻለን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ መስዋዕትነት ተከብራ ትኖራለች !

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.